top of page
Writer's pictureOLA Command

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመንግስት ፍቃድና ድጋፍ እየተወሰደ ያለውና በኦሮሞዎች ላይ ያነጣጠረው የዘር ማፅዳት ዘመቻ እናወግዛለን።

(የኦነግ-ኦነሠ ጋዜጣዊ መግለጫ)

በአብይ አህመድ እና ጽንፈኛ የአማራ ሃይሎች በኦሮሞ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ብሄር ተኮር የዘር ማጥፋት ዘመቻ በተጠናከረ መልኩ ቀጥሏል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተለይ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ሃይል እና ፋኖ የሚባሉ የተደራጁ የአማራ ሽፍቶች የሸብር ተግባር መፈንጫ ከሆነ ውሎ አድሯል። እነዚህ ሃይሎች ይህን ክልል የንፁሀን ኦሮሞዎች፣ የትግራይ ተወላጆች እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተወላጆች የጅምላ ግድያና መቃብር ቀጠና እንዳደረጉትና በተለይም የአማራ ልዩ ሃይል እና የፋኖ ታጣቂዎች ንፁሀን ዜጎችን እየጨፈጨፉ እና የተጎጂዎችን ንብረት እየዘረፉ መሆኑን ደጋግመን ዘግበናል። ነገር ግን ይህ መንግስታዊ አሸባሪነት አሁንም ተጠናክሮ ተናቦና ተወሳስቦ ቀጥሏል።

ማክሰኞ መጋቢት 22 ቀን 2022 (እኤአ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዲባጤ ወረዳ እነዚህ የአማራ ሽፍታ ሃይሎች አምሳሉ አመንቴ የተባለ የኦሮሞ ወጣት ከህግ አግባብ ውጪ በመግደል ንብረቱን ዘርፈዋል። ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ኦሮሞዎችን በዘር ለማፅዳት ባለመ ሌላ ግልጽ ሙከራም 50 የሚጠጉ የኦሮሞ ቤቶችን በእሳት ያጋዩ ሲሆን በዚህ አረመኔያዊ እርምጃ ምን ያህል ሰዎች ከነቤታቸው እንዳለቁ በግልፅ ባይታወቅም እስካሁን ድረስ ጥቂት አስከሬኖች ከአመድ ውስጥ ተለይተዋል:: እነዚህ የዘር ማጥፋት ሃይሎች ከ200-400 የሚደርሱ ወታደሮችን በቡድን በማደራጀት ከፌደራልና ከሶስቱ ክልሎች ማለትም የአማራ: የኦሮሚያና ቤኒሻንጉል ጉምዝ የመንግስት ባለስልጣናትም ጋር በመቀናጀት በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ እርምጃዎችን እየወሰዱ እንደሆነም ከቦታው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ማክሰኞ መጋቢት 15 ቀን 2022 ብርሃኔ ረጋሳ የተባለች ነፍሰ ጡር እና የሰባት ልጆች እናት በሌላ ዙር የድንጋይ ዘመን አረመኔያዊ ድርጊት በአማራ ታጣቂዎች በኦሮሞነቷ ብቻ አንገቷ ታርዶ መገደሏ የሚታወስ ሲሆን ይህ ድርጊት የዚህ ፅንፈኛና ጨካኝ ቡድን ልዩ መለያ እየሆነም መጥቷል። በተመሣሣይ ሁኔታም ከሁለት ቀናት በኋላ መጋቢት 17 ቀን 2022 በቤኒሻንጉል ክልል ዲባጤ ወረዳ ቢሻን አዲ እየተባለ በሚጠራው ቦታ የታፈኑት 18 የኦሮሞ ተወላጆች እስካሁን የደረሱበት አልታወቀም። ከነዚህም ውስጥ አስራ ሁለቱ ተማሪዎች (ኮልቴ ፈይሳ፣ ታረቀኝ አርጋታ፣ ደበላ ሥዩም፣ ረጋሳ ባጎንጆ፣ ጀቤሳ ተሾመ፣ ገፄ ከበደ፣ አያንቱ ገመቹ፣ ኃይሌ በሴ፣ እምነት ጋሮማ፣ ከፍያለው ዋቅጅራ፣ ጃለኔ ገመቹና ፈይሳ መኮንን) ማንነታቸው ሲታወቅ ሌሎች ስድስት ሰዎች ማንነታቸው በውል አልታወቀም::

የአብይ አህመድ የጸጥታ ሃይሎች እና አጋዥ የአማራ ፅንፈኛ ሀይሎች በቤኒሻንጉል በርካታ ተወላጆችንና ነዋሪዎችን በተደጋጋሚ ሲገድሉ ሲያፍኑና ሲዘርፉ በተለይም በቅርቡ የትግራይ ተወላጆችን ከነህይዎታቸው በማቃጠል ወደ ሌላ አረመኔያዊነት ደረጃ ሲሸጋገሩ ራሱን መንግሥት ነኝ እያለ የሚጠራው የብልፅግና ቡድን ጆሮ ዳባ ልበስ ከማለቱም በላይ በድርጊቱ እየተባበረ ቀጥሏል።

አለም አቀፉ ማህበረሰብ የነዚህን የአማራ ተስፋፊና የአብይ አህመድ "የጸጥታ" ሃይሎች ፀረ ሰብአዊነት እርምጃ እንደ በመንግስታዊ ሽብር እንዲፈርጅ አሁንም ደግመን እንጠይቃለን። በተጨማሪም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሰላማዊ ዜጎችን ከጅምላ አሰቃቂ ወንጀሎች የመጠበቅ ሃላፊነቱን በመገንዘብ በንፁሀን ዜጎች ላይ ሽብር የሚፈፅመውንና የሚያስፈፅመውን የዚህን ፋሺስታዊ አገዛዝ አቅም በመገደብ ረገድ የበኩሉን ድርሻ መወጣት አለበትም እንላለን። ቢያንስ የአገዛዙ አለም አቀፍ አጋሮች የአገዛዙን የገንዘብ አቅም በእቀባ በማዳከም ለሽብር ተግባሩ የሚያውለውን ወታደራዊና የመረጃ አቅም በማሽመድመድ ንፁሀንን መታደግና ሀገሪቱንም ከበለጠ ደም መፋሰስ ማዳን እንደሚቻል የኦነግ - ኦነሠ ደጋግሞ ያሳስባል:: በተመሳሳይም የአገዛዙ አለማቀፍ አጋሮች ለአብይ አህመድ እና የወንጀል አጋሩ የሆነው የኤርትራ መንግስት የጦር መሳሪያ ሽያጭን ወይም ማስተላለፍን ማስቆም የሚያስችል ህግ ማውጣትና መተግበር እንዳለባቸው በሰብአዊነት ለሚያምኑ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ አባላትና አካላት አቤቱታችንን እናቀርባለን።

በመጨረሻም ይህ በሕዝባችን ሰብአዊነትና ክብር ላይ የሚፈፀመው አረመኔያዊ ጥቃት አፀፋዊ ምላሽ ሳያገኝ እንደማይቀርና ወንጀለኞችም ለፍትህ አደባባይ እንደሚቀርቡ በእርግጠኝነት እየገለፅን ኦነግ - ኦነሠ ይህ እውን እንዲሆን በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ለህዝባችን ደግመን እናበስራለን።

ፍትሕ ለተጎዱት ሁሉ! ድል ለኦሮሞ እና ለተጨቆኑ ህዝቦች በሙሉ! የኦነግ-ኦነሠ ከፍተኛው ዕዝ መጋቢት 28 ቀን 2022

8 views0 comments

Recent Posts

See All

Comments


bottom of page